ዘመን ባንክ ከ 1.8 ቢሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡን ገለፀ
(ካፒታል : ህዳር 23፤2016 ዓ.ም.)
ዘመን ባንክ በተያዘው በጀት ዓመት 1.81 ቢሊዮን የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ገልፆ ካለፈዉ ዓመት አንፃር 336 ሚሊዮን ብር ብልጫ ማሳየቱንና 22.8 በመቶ እድገት አሳይቷል ብሏል።
የባንኩ አማካይ የተከፈለ ካፒታልን መሰረት በማድረግ ለባለአክሲዮኖች የትርፍ ድርሻ 31.1 በመቶ መሆኑን አሳዉቋል።
ዘመን ባንክ 47.8 ቢሊዮን ደርሷል ያለዉ ጠቅላላ ሀብቱ ለተለያዩ ክፍላተ ኢኮኖሚያዎች የተሰጠው ብድር 31.4 ቢሊዮን ከፍ ማድረግ ችያለሁ ሲል በሪፖርቱ ገልጿል።
ካፒታል በተመለከተዉ ዓመታዊ ሪፖርት ባንኩ በዓመቱ ከታቀደዉ እቅዱ 95 በመቶ አሳክቻለሁ ባለዉ አጠቃላይ ገቢዉ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 5.74 ቢሊዮን ደርሷል፤ ለዚህም ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው የወለድ ገቢ 3.99 ቢሊዮን (69.6 በመቶ) ሲሆን የአገልግሎት ክፍያ እና የኮሚሽን ገቢጰ1.32 ቢሊዮን (23.1 በመቶ) ነዉ ብሏል።